በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ሰርጸትና ማህበረሰብ ጉባኤ ተጀመረ

74

ሐረር፤ መጋቢት 30/ 2013 (ኢዜአ) በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የምርምር ሰርጸትና ማህበረሰብ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ።

በጉባኤው በጤና ፣ ግብርና ፣ ቴክኖሎጂ ፣ማህበረሰብ ሳይንስ ጨምሮ የተለያዩ 75 የምርምር ፕሮጀክቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይና በማህበረሰቡ ላይ የተከናወኑ የድጋፍ ስራዎችም እንደሚቀርቡ ተመልክቷል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ተመራማሪዎች ፣ የምርምር ተቋማት እንዲሁም  የሐረሪ ክልል ፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተወካዮች ተሳታፊ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም