ቀጥታ፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ መጋቢት 30 ቀን 2013 (ኢዜአ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብን ይፋ አደረገ።

ዛሬ ይፋ በተደረገው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት መሰረት በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ፈተና ወስደው 380 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ወንድ ተማሪዎች እንዲሁም 368 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

በዚሁ የትምህርት መስክ ለታዳጊና አርብቶ አደር ክልሎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ለወንዶች 368 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች ደግሞ 358 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።

ለአካል ጉዳተኞች ዓይነ ስውራንና መስማት የተሳናቸው ወንዶች 350 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 345 እና ከዚያ በላይ ውጤት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሆኗል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለወሰዱ ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 358 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 350 እና ከዚያ በላይ የመግቢያ ነጥብ ነው።

በተመሳሳይ በሶሻል ሳይንስ የትምህርት መስክ ፈተና የወሰዱ ወንድ ተማሪዎች 370 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት ተማሪዎች 350 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል።

በታዳጊና አርብቶ አደር ክልሎች ደግሞ ወንዶች 358 እና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 348 እና ከዚያ በላይ ውጤት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ነጥብ ሆኖ ተቀምጧል።

የአካል ጉዳተኞች ዓይነ ስውራንና መስማት የተሳናቸው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ወንዶች 348 እና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 335 እና ከዚያ በላይ ነጥብ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ለሚገኙ ተፈታኞች ለወንዶች 348 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 340 እና ከዚያ በላይ ውጤት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሆኗል።

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ባልሆኑ ፕሮግራሞች ማለትም በማታ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ፣ በርቀት፣ በበይነ መረብና በግል ተቋማት በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ አማራጮች ለመማር አነስተኛው የመቁረጫ ነጥብ ለወንዶች 330 እና ከዛ በላይ፣ ለሴቶች 320 እና ከዛ በላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

2

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም