ቀጥታ፡

የሁለተኛ ዙር የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ነገ ይጀመራል

መጋቢት 26/2013 (ኢዜአ) የሁለተኛ ዙር የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድር ነገ ይጀመራል።

በሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ጌታ ዘሩ ስፖርት ክለብ፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ ፌደራል ማረሚያ ቤቶችና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

 የአምስተኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ነገ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ  በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።

ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ30  ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከአዲሱ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ከጠዋቱ 3 ሰአት ከ30 ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከጌታ ዘሩ ስፖርት ጋር ይጫወታሉ።

የሁለተኛ ዙር የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እስከ ግንቦት 5 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ12 ነጥብ ሲመራ፤ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በዘጠኝ ነጥብ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በስድስት ነጥብ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያለ ምንም ነጥብ በሊጉ ግርጌ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም