ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21 /2013 (ኢዜአ) በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ።

ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈው ኒጀርና ማዳጋስካር ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን በማጠናቀቃቸው ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከኮትዲቯር አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት እየተመራ የመሃል ዳኛው በህመም ሳቢያ አቋርጦ ወጥቷል።

ቡድኑ በ9 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ካሜሩን ለምታስተናግደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ማለፉን አረጋግጧል።

ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ የአሁኑ ለ11ኛ ጊዜ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈው እ.አ.አ በ2013 ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ መሆኑ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም