ቀጥታ፡

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ መጋቢት  21/2013  ( ኢዜአ) ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ግንባታ የሚሆን 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ፋብሪካው ድጋፉን ያደረገው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለቱሪዝም ዘርፍ እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ እንዲሁም ልማት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ፋብሪካው በቀጣይም ማህበራዊ ሃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የአገሪቷን ልማት በመደገፍ በኩል የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል።

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ባለፉት 20 አመታት ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ በስራ እድል ፈጠራ፣ በጤና ተቋማት ግንባታና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተዋፆ ማድረጉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም