ለመንግስት አገልግሎት ጥራት እውቅና እየተሰጠ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለመንግስት አገልግሎት ጥራት እውቅና እየተሰጠ ነው
መጋቢት 18/2013 (ኢዜአ) የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እውቅና የሚሰጥበት መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ያዘጋጀው ልዩ ውድድር የማጠቃለያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በሁለቱ ተቋማት አማካኝነት ለመወዳደር ፍቃደኛ ሆነው የተገኙ 10 የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እውቅና የሚሰጣቸው ይሆናል።
ሳይንስና ኢኖቬሽን፣ ገቢዎች፣ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴሮች፤ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣንና የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት እውቅና ከሚሰጣቸው መካከል ናቸው።
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የፌዴራል መካከለኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግም እንዲሁ።
በእውቅና መስጠት መርሃ-ግብሩ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነርና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።