ቀጥታ፡

“የናይል ተፋሰስ ኢንቨስትመንቶችን እንደገና ማጤን” በሚል 6ኛው የናይል ተፋሰስ የልማት ፎረም ሊካሄድ ነው

መጋቢት 17 ቀን 2013 (ኢዜአ) “የናይል ተፋሰስ ኢንቨስትመንቶችን እንደገና ማጤን” በሚል 6ኛው የናይል ተፋሰስ የልማት ፎረም በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እንደሚካሄድ የውሐ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በናይል ተፋሰስ አጋራት ልማት ላይ የሚያተኩረው የናይል ተፋሰስ አገራት ስድስተኛውን የልማት ፎረም ኢትዮጵያ እንደምታዘጋጅ የውሐ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።

አጀንዳውም “የናይል ተፋሰስ አካባቢ ኢንቨስትመንቶችን እንደገና ማጤን” የሚል ሲሆን በተፋሰሱ አጋራት የውሐ፣ የኃይል፣ የምግብ ፣ የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ላይ እንደሚያተኩር ታውቋል።

በዌብናር በሚካሄድ ውይይት መርሐግብሩ እንደሚከናወን ነው የተነገረው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም