ቀጥታ፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፋችን ይቀጥላል - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ መጋቢት 15/2013 (ኢዜአ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት ከሚያከናውናቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አንዱ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ትናን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የግድቡ ገንባታ በርካታ ውጣ ውረዶች ቢኖሩትም በስኬት ይጠናቀቃል ብለዋል።

በግድቡ ግንባታ የትኛውንም አገር የመጉዳት አላማና ፍላጎት የለንም እንዳውም በጋራ የመልማት ፍላጎት ኖሮን እየሰራን ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግድቡ ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ መንግስት ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት ያለውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የግድቡ ግንባታ ስኬት የኢትዮጵያ ህዝቦች ትብብርና እገዛ ያልተለየው መሆኑን ያነሱት ነዋሪዎቹ በቀጣይነት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በጤና፣ በትምህርትና በሌሎች መስኮች የተጀመሩ ፕሮጀከቶች እንዲጠናቀቁም  የድርሻችንን ለመወጣት ዘግጁ ነን ብለዋል።ለቀጣይትውልድየተሻለነገርለማቆየትየግድቡግንባታ ስኬት ወሳኝመሆኑንም ገልጸዋል።

 ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል አቶ ፍሥሐ ንጋት እና መምህር ዘለዓለም እጅጉ እንዳሉት የህዳሴው ግድብ  ግንባታ  በአሰቸጋሪ ወቅት ላይ  እንካ መቀጠል አለበት ለዚህም የመንግሥትኔ እየሰራ አድንቀዋል።

አቶ ፍሥሐ ንጋትና ወጣት አሸናፊ ለማ  በበኩላቸው  መንግሥት  በመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ በተለይ በትምህርት ዘርፍ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚያስመሰግነው መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም