ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማዳጋስካር አቻውን 4 ለ 0 አሸነፈ

ባህርዳር ፤ መጋቢት 15/2013 (ኢዜአ) ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ በባህርዳር ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማዳጋስካር አቻውን አራት ለዜሮ አሸነፈ።

የማዳጋስካር አቻውን ማሸነፍ የቻለው አማኑኤል ገብረማርያም፣ ጌታነህ ከበደ፣ አቡበከር ናስር እና ሽመልስ በቀለ በስቆጠሯቸው   ጎሎች ነው።

በጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  ኳስን ይዞ በመጫወትና ወደ ጎል በመጠጋት ተጽእኖ ፈጥሯል።

ከእረፍት በኋላ ግን የማዳጋስካር ብሄራዊ ቡድን  ጠንካራ እንቅስቃሴ በማካሄድ ጎል ለማስቆጠር ተደጋጋሚ  ሙከራዎችን ቢያደርግም በበረኛው ከሽፎበታል።

በዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አራት ለዜሮ  ለማሸነፍ ያስቻለውን ውጤት አስመዝግቧል።

ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ ያስመዘገበው ውጤት በቀጣይ  የሚያካሂደውን ጨዋታ በበላይነት አጠናቆ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ብርታት እንደሚሆነው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ማዳጋስካር ተጉዞ  አንድ  ለዜሮ  በሆነ ውጤት ተሸንፎ መመለሱ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም