ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ "ሐ" የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ቀጥሎ ትናንት ሶስት ጨዋታዎች ተካሄደዋል

ነቀምቴ ፤ መጋቢት 15/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ "ሐ" የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ትናንት ነቀምቴ በሚገኘው የወለጋ ስታዲዮም ቀጥሎ ሶስት ጨዋታዎች ተካሄደዋል ፡፡

ጥዋት ላይ በተካሄደው የአርባ ምንጭ ከነማ እና ባቱ ከነማ የእግር ኳስ ክለቦች ጨዋታ ያለምንም ግብ ተለያይተዋል፡፡

ከሰዓት በኋላ  በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮ -መድን አርሲ ነገሌን ሶስት ለአንድ ሲያሸንፍ፣ ቀጥሎ የተገናኙት  የካ ክፍለ ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ  ያለምንም ግብ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

መጋቢት 13/2013ዓ.ም. የተጀመረው የውድድሩ ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ  የሚገቡ ቡድኖችን ለመለየት በ12 ክለቦች  መካከል የሚካሄድና  ለ45 ቀናት  የሚቆይ መሆኑን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን  የውድድሩ  አስተባባሪ አቶ ኃይሉ ምህረት አየሁ  ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም