የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ "ሐ " የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ "ሐ " የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ተጀመረ
ነቀምቴ ፤ መጋቢት 14/2013 (ኢዜአ) ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ " ሐ " የክለቦች እግር ኳስ ውድድር በወለጋ ስታዲዮም ተጀመረ።
ውድድሩ በ12 ክለቦች መካከል እንደሚካሄድና ለ45 ቀናት እንደሚቆይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የውድድሩ አስተባባሪ አቶ ኃይሉ ምህረት አየሁ ገልጸዋል።
ውድድሩ በየቀኑ በሶስት ክፍለ ጊዜ ተከፍሎ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋና የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባህሩ ኤባ በቦታው ተገኝተው ውድድሩን ትናንት ሲያስጀምሩ የተገናኙት ጌዲኦ ዲላና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ክለቦች በአንድ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የጌዲኦ ዲላ ስፖርት ክለብ ፕሬዚዳንት አቶ ተዘራ ጌታሁን በሰጡት አስተያየት የነቀምቴ ከተማና አካባቢው ነዋሪ ህዝብ በፍቅር ተቀብሎ እንዳስተናገዳቸው ተናግረዋል።