ቀጥታ፡

የለውጡ ሂደት ተምረው አገራቸውንና ራሳቸውን ለመለወጥ ጥረት ለሚያደርጉ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ... ተማሪዎች

አዲስ አበባ ሐምሌ 21/2010 በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የለውጥና የአንድነት ጉዞ ተምረው አገራቸውንና ራሳቸውን ለመለወጥ ጥረት ለሚያደርጉ ኢትዮጵያውን ትልቅ ሚና ይኖረዋል ሲሉ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ተናገሩ። ዩኒቨርሲቲው በ35ኛው ዙር በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ በ21 የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1ሺህ 325 ተማሪዎች ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ ውስጥ 206 ትምህርታቸውን የጨረሱት በማዕረግ ነው። ከተማራቂዎች መካከል 1 ሺህ 188 በቅድመ ምረቃ ሲሆኑ 137ቱ ደግሞ የድህረ ምረቃ ትምህርት ያጠናቀቁ ናቸው። በተመሳሳይ በመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤቱ በቅድመ መደበኛ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 161 ህፃናትንም ማስመረቅ ችሏል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተመራቂዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተጀመረው የለውጥ መንገድ ለተማሪዎች መነሳሳትን የፈጠረና የተሻለ ስራ ለመስራት መንገድ የሚከፍት እንደሆነ ተናግረዋል። የዋንጫ ተሸላሚ ኤፍሬም በየነ አሁን የተፈጠረው አገራዊ አንድነትና ሰላም በላሀብቱን በመሳብ የስራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ስራ ፈጥሮ ለመስራትም ለሚመጣው ትውልድ ጠቃሚ እንደሆነ እምነቱን ገልጿል፡፡ ከሶስት መቶ ሃምሳ እስከ አራት መቶ የኢትዮጵያ ምሁራን የተሳተፉት መሆኑን ገልጻ ይህን ያህል ኢትዮጵያችን ወርቅ ካላት የተሻለ ቦታ በመሄድ የመማር የመለወጥ አገርን የመርዳት ስሜት ያሳድራል ያለችው የዋንጫ ተሸላሚ ብስራተገብርኤል ናት፡፡ “ይሄ ዘመን የመደመር ዘመን ብቻ ሳይሆን የመንጠርም ዘመንም ይመስለኛል” ያሉትወይዘሮ ራሄል መኩሪያ እውነተኛ የህዳሴ ዘመን የሚመጣ፤ በአግዚአብሄር እርዳታና ከህዝቡ ጋር ተባብረን በመስራት እውነተኛ መለወጥ፤ እውነተኛ መደመርና መሻገር እንዲሆን ልባዊ ምኞታቸው መሆኑን ተጋግረዋል፡፡ የለውጡ አስጀማሪና አንቀሳቃሽ ከመሆን ባለፈ ለተማሩት ዜጎች እውቅና ለሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች እያስተማረና እያሰለጠነ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው ከማስተማር በተጨማሪ 340 ለሚጠጉ የከፍተኛና የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች የነጻ ትምህርት እድል መስጠቱ ተጠቁሟል። በዛሬው የምረቃ ስነስርዓት ለፕሮፌሰር ደስታ ምክሩንና የህብረትኢንሹራንስ መስራቹ አቶ ኢየሱስ ወርቅዛፉ የላቅ ውጤት ሽልማት ሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲው ከከፍተኛ ትምህርት በተጨማሪ ከመዋለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በአዲስ አበባ ገርጂና ጦር ኃይሎች እንዲሁም በአዳማ ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን በ2011 ከ9ኛ እስከ 12ኛ ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገልጿል። በከፍተኛ ትምህርትም በ2011 ሁለት የድህረ ምረቃና ሁለት የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም