ሉሲዎቹ በሴካፋ ውድድር የጸባይ ዋንጫና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል - ኢዜአ አማርኛ
ሉሲዎቹ በሴካፋ ውድድር የጸባይ ዋንጫና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል
አዲስ አበባ ሀምሌ 21/2010 በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ውድድር ሉሲዎቹ ሶስተኛ ደረጃ ይዘው በማጠናቅቅ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በትናንትናው እለት ከታንዛኒያ አቻው ጋር በነበረው ጨዋታ ማሸነፍ ቢችል ዋንጫውን የማንሳት ዕድል ነበረው። ቡድኑ በትናንት ጨዋታ በታንዛኒያ 4 ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። ሉሲዎቹ የትናንቱን ጨዋታ መሸነፋቸውን ተከትሎ ታንዛኒያ ሰባት ነጥብ በሰባት ነጥብ ዋንጫውን ለማንሳት ችላለች። ተመሳሳይ ሰባት ነጥብ ያላት ኡጋንዳ በግብ ክፍያ ተበልጣ ውድድሩን ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። ሉሲዎቹ ደግሞ ስድስት ነጥብ በመሰብስብ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪ የውድድሩን የጸባይ ዋንጫ አግኝተዋል። ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ውድድር ከተሳተፉት አምስት አገሮች መካከል ከንያና ርዋንዳ እንደየቅደም ተከተላቸው አራተኛና አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል።