ቀጥታ፡

በድህነት ውስጥ ያሉ ሴቶች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ሁሉም ሊሰራ ይገባል ..ፊልሰን አብዱላሂ

መጋቢት 11/2013(2013(ኢዜአ) በአገሪቱ በድህነት ውስጥ ያሉ ሴቶች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ሁሉም ሊሰራ እንደሚገባ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ገለጹ።

"የሴቶችን መብት የሚያከብር ማኀበረሰብ እንገንባ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ የሚገኘውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በብሄራዊ ቴአትር ቤት ያዘጋጀው ታላላቆች የሚታደሙበት መሰናዶ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ፣ የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የተለያዩ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ሴት ካፒቴኖችና ሰራተኞች፣ ሴት የመከላከያ ሰራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ አባላትና ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ ሴቶችም በመድረኩ ታድመዋል።

በመድረኩም "የገጠሯ ሴት የቀን ውሎ" የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ለእይታ ቀርቦ በታዳሚዎች ሀሳብ ይሰጥበታል ተብሏል።

ዘጋቢ ፊልሙ በ10 ክልሎች ገጠር ያሉ ሴቶችን ውሎ የሚያሳይ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ሙና አህመድ ናቸው።

መንግስት የሴቶችን የኢኮኖሚተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ኀብረተሰቡ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም