ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማላዊ አቻውን 4 ለ 0 አሸነፈ

መጋቢት 8 ቀን 2013 (ኢዜአ) ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማላዊ አቻውን 4 ለ 0 አሸነፈ።

ቡድኑ ከማላዊ አቻው ጋር በባህርዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ መስኡድ መሀመድ፣ ጌታነህ ከበደ፣ ሱራፌል ዳኛቸውና አቡበከር ናስር ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ሊወጣ ችሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማዳጋስካር እና ከኮትዲቯር ላለበት ጨዋታ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም