የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ከሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር እስካሁን በተከናወኑ የምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከረ ነው።
የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በሚመሩት የውይይት መድረክ ፓረቲዎች በእጩዎች ምዝገባ ያቀረቧቸው ቅሬታዎችና የተሰጡ መፍትሄዎችን በሚመለከት ሪፖርት ቀርቧል።
በውይይት መድረኩ በሂደቱ አስካሁን ያጋጠሙ ችግሮችና ስኬቶች ተነስተው ምክክር እንደሚደረግባቸውም ይጠበቃል።