ቀጥታ፡

አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ ከሱዳን የስደተኞች ተጠባባቂ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

መጋቢት 6 ቀን 2013 (ኢዜአ) በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ ከሱዳን የስደተኞች ተጠባባቂ ኮሚሽነር ኢብራሂም አብደላ ጋር በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን በተመከለተ መወያየታቸውን ገለጹ።

አምባሳደር ይበልጣል ከኮሚሽነሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውን ስደተኞ ወቅታዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስልና እየተካሄዱ ያሉ የድጋፍ ስራዎችን በተመለከተ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

በሱዳን የሚገኙ ዜጎች በፈቃደኝነት ወደ አገራቸው በሚመለሱብት ሁኔታ ዙሪያ መወያየታቸውንም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም