ቀጥታ፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሜቴ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ጌታቸው አስክሬን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ሐምሌ 21/2010 የብአዴን ማዕከላዊ ኮሜቴ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ጌታቸው አስክሬን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ። አስክሬናቸው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢህዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተቀብለውታል። አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በአሜሪካ የህክምና ክትትል ለማድረግ ባመሩበት ወቅት ነበር ህይወታቸው ያለፈው። ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ የገባው የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው አስክሬን በመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ወደ ባህር ዳር ከተማ አሸኛኘት ተደርጎለታል። የቀብር ስነስርዓታቸውም ዛሬ ከቀኑ 7፡00 በባህር ዳር ይፈጸማል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም