ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በምዕራብ አርሲ ዞን ኤበን አርሲ ወረዳ ሾባ ቡልቱም ቀበሌ በመስኖ የለማን የስንዴ ሰብል ጎበኙ

132

መጋቢት 4/2013 ዓም (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በምዕራብ አርሲ ዞን ኤበን አርሲ ወረዳ ሾባ ቡልቱም ቀበሌ በመስኖ የለማን የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል።

በዚህ ጉብኝት ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በዚህ በኤበን አርሲ ወረዳ 1 ሺህ 5 መቶ ሄክታር መሬት በስንዴ ምርጥ ዘር መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ገለቶ ገልጸዋል።

ሃላፊው ለኢዜአ እንደገለጹት በወረዳው ከስንዴ በተጨማሪ 4 ሺህ ሶስት መቶ ሄክታር መሬት በሽንኩርት፤ቲማቲም ፤ ድንች እና በሌሎች ምርቶች ተሸፍኗል።

በአካባቢው ለመጀመሪያ ጊዜ መስኖን በመጠቀም የግብርና ስራው ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች መንግስት የትራክተር፤ ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም