ቀጥታ፡

የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት አስመልክቶ በመቀሌ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

መቀሌ ሐምሌ 21/2010 በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ሰላም በመደገፍ  የመቀሌ ከተማና አከባቢው ህዝብ  ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ነዋሪዎቹ የኢትዮጵያና የትግራይ ክልል ባንዴራዎችና የህወሓት አርማን አንግበው ሰልፉ ወደ ሚካሄድበት የትግራይ ክልል ስታዲዮም የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ገብተዋል። ሰልፈኞቹ ካሰሰሟቸው መፈክሮች መካከልም "ሁሉም ዓይነት ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተፈጠረው ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረው በቁርጠኝነት እንሰራለን፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱና የህግ ልእልና ይከበር የሚሉት ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም