አቡዳቢ ፊውቸር ኢነርጂ የተሰኘ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከጸሃይ ሃይል ለማልማት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ - ኢዜአ አማርኛ
አቡዳቢ ፊውቸር ኢነርጂ የተሰኘ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከጸሃይ ሃይል ለማልማት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ መጋቢት 3/2013 አቡዳቢ ፊውቸር ኢነርጂ የተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከጸሃይ 500 ሜጋ ዋት ሃይል ለማልማት የሚያስችልውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
በስምምነቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ መሐመድ እስማኤል ጀማል አል-ራሚፍ ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው የኃይል ልማቱን የሚያካሂደው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይል ምቹ መሆኗን ጠቅሰው ከዚህ አንጻር ኩባንያው በኢነርጂ ዘርፍ ለመሳተፍ መወሰኑ ተገቢ ነው ብለዋል።
መንግስት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።