በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ - ኢዜአ አማርኛ
በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
መጋቢት 3-2013 ዓም (ኢዜአ) በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ያለውን ትክክለኛ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅና በኢትዮጵያ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ተገቢ ያልሆኑ ጫናዎችን ለመቃወም የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።
ሰልፈኞቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ም/ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንዲያከብር ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ ላይ ሆን ተብሎ እየተነዙ ባሉ የተሳሳቱ መረጃዎች ሰለባ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባቸውን በሚዛናዊነት እንዲሰሩ በሰልፉ ላይ ተጠይቋል።
እንዲሁም የሱዳን መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መግባቱን አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገልጸዋል።