ቀጥታ፡

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

መጋቢት 1 / 2013 (ኢዜአ) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት በመገኘት መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

በሰልፉ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ባሰሙት መፈክር አሜሪካ ያሳየችው ጣልቃ ገብነት የተሳሳተ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ ‘ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣ በኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት አመታት ለተፈጸመው ጥፋት ተጠያቂው የህወሃት ወንጀለኞች ቡድን ነው፣ ግድቡ የእኔ ነው፤ እንደጀመርኩ አጠናቅቀዋል፣ ስልጣን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንጂ በጠመንጃና በአሸባሪነት መያዝ አብቅቷል፣ በትግራይ ህዝቡ ወደተለመደ ኑሮው እንዲመለስ መንግስት የጀመረውን ጥረት እንዲያጠናክር እንጠይቃለን፣ ...’ የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም