ቀጥታ፡

የጅማ ዞን የወረዳዎች ዘመናዊ ስፖርት ሻምፖዮና በአጋሮ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ጅማ ፣የካቲት 28/2013 (ኢዜአ) ለአስራ አምስት ቀናት የተካሄደው የጅማ ዞን የወረዳዎች የዘመናዊ የስፖርት ሻምፕዮና በአጋሮ ከተማ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

የእግርና የመረብ ኳስ፣ አትሌቲክስ ፣ጠረጴዛ ቴንስን ጨምሮ በአስር የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የቆየው ውድድር ትላንት ተጠናቋል።

የዞኑ ሰፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነጉማ መኮንን ለኢዚአ እንደገለጹት በውድድሩ አጋሮ ከተማ አምስት ዋንጫዎችን በማግኘት አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

በመዝጊያ ስነ ስርአቱ  በሁለት ዲቪዚዮኖች የእግርና የመረብ ኳስ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በአንደኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ቦተር ጦላይ ወረዳ ዋንጫ ሲወስድ በሁለተኛ ዲቪዚዮን ደግሞ ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ቦተር ጦላይ ወረዳ በወንዶች በእግር ኳስና በመረብ ኳስ ዋንጫ ሲወስድ በሴቶች የመረብ ኳስ ደግሞ የቀርሳ ወረዳ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱላኪም ሙሉና የኦሮሚያ የጠቅላላ ስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ጉርሙ ለአሸናፊ ቡድኖችን የዋንጫና ሌሎች ሽልማቶችን አበርክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም