ሉሲዎቹ በሴካፋ ውደድር በታንዛኒያ በመሸነፋቸው የዋንጫ እድላቸውን አምክነዋል - ኢዜአ አማርኛ
ሉሲዎቹ በሴካፋ ውደድር በታንዛኒያ በመሸነፋቸው የዋንጫ እድላቸውን አምክነዋል
አዲስ አበባ ሀምሌ 20/2010 በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ለሶስተኛ ጊዜ በምስራቅና መካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ (ሴካፋ) ውድድር ሉሲዎቹ በታንዛኒያ አቻቸው 4 ለ 1 ተሸንፈው ዋንጫ እድላቸውን አምክነዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በመጀመሪያው አጋማሽ በመሰሉ አበራ ቀዳሚ ቢሆንም ታንዛኒያዎች በሁለተኛው አጋማሽ በ47፣ 53፣60ኛውና 90 ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው አራት ጎሎች 4 ለ 1 አሸንፈዋል። ይህን ተከትሎም ታንዛኒዎቹ በሰባት ነጥብና በአምስት ጎል ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቃቸው ዋንጫውን የማንሳት እድላቸው ከፍተኛ ነው። የታንዛኒያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋንጫውን ለማንሳትም ከደቂቃዎች በኋላ የሚደረገውን የሩዋንዳና ኪንያ ጨዋታን እየጠበቁ ነው። ምንም እንኳ ሩዋንዳ በሂሳብ ስሌት መሰረተ ዋንጫውን የማንሳት እድል ቢኖራትም አራት ነጥብ ሁለት ግብ እዳ ያለባት በመሆኑ ዋንጫውን ለመውሰድ ኬኒያን ከሰባት የጎል ልዩነት በላይ ማሸነፍ ግድ ይላታል። የሩዋንዳ ተጋጣሚ የሆነችው ኬኒያ ደግሞ ይህን ጨዋታ ብታሸንፍም ሆነ አቻ ብትወጣ ዋንጫ የማንሳት እድል የላትም።