ኬንያ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንድታዘጋጅ ተመረጠች

71
አዲስ አበባ ሃምሌ 20/2010 ኬንያ በ2020 18ኛውን ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንድታዘጋጅ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር መረጣት። ውድድሩ በአፍሪካ ምድር ተካሄዶ አያውቅም ፤ ኬንያ ዕድሉን ያገኘች የመጀመሪያ አፍሪካዊት አገር ናት። ኬንያ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ባለፈው ዓመት የዓለም ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተሳካ መልኩ ማስተናገዷ አሁን አንድትመረጥ እንዳደረጋት ማህበሩ አስታውቋል። የዓለም የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዝዳንት ሰባስትያን ኮ እንደተናገሩት "የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና የቀጣይ ስፖርቶኞቻችን የምናይበት መድረክ ነው፤ ኬንያ ደግሞ በአትሌቲክስም ብዙ ታሪክ ያላት አገር ስለሆነች የአዘጋጅነት ዕድል ማግኘቷ ተገቢ ነው።" በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር  ከሁለት ሳምንት በፊት በፊላንድ መደረጉ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ 3 ወርቅ፣ 2 ብርና 4 ነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን በመያዝ ከዓለም አራተኛ ስትሆን፤ የማስተናገድ ዕድል የተሰጣት ኬንያ ደግሞ በ6 ወርቅ፣ 4 ብርና አንድ ነሐስ  በድምሩ 11 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም አንደኛ ሆና መጨረሷ አይዘነጋም፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም