ቀጥታ፡

የምድራችን ለአደጋ የተጋለጠ የጎሪላዎች መኖሪያ

የካቲት 24/2013 በአፍሪካ አንጋፋና ትልቁ የዲሞክራቲክ ኮንጎ የቨርንጋ ብሄራዊ ፓርክ በምድራችን ላይ  ለአደጋ  የተጋለጠ  ለሰራተኞቹ ምቹ ያልሆነ ፓርክ  መሆኑን  ተነገረ፡፡

በዘገባው ባለፈው ሳምንት  በፓርኩ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት የጣሊያን አምባሳደር ፣ የጥበቃ ሰራተኛውን እና ሾፌሩን በስፍራው ከሚንቀሳቀሱ አማፅያን  በተተኳሰ  ጥይት መገደላቸውን   አስታውሷል  ፡፡

በዚሁ ፓርክ ባለፉት አንድ አመት ውስጥ ከ20 በላይ የፓርኩ የጥበቃ ሚሊሻዎች ተገድለዋል፡፡ የሞቱት ሰዎች በሙሉ ዕድሜያቸው ከ 25 እስከ 30  እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

የፓርኩ ሐይቆች ኃላፊ የሆኑት ግራፊየን ሙይሳ ሲቫንዛ  “በእውነቱ ብዙ ወጣቶችን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ  ማጣት  በጣም  ያሳዝናል” ብለዋል ፡፡

በዚህ አንጋፋ ብሔራዊ ፓርክ ከ 800 በላይ የደን ጠባቂዎችን በኃላፊነት የሚመራው ኢማኑኤል  ዴ ሜሮዴ ይህንን ሥራ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የተከፈለው መስዋእትነት ከፍተኛ መሆኑን ያስረዳል፡፡

ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ወገኖቼ ሥራቸውን በጣም ከመውደዳቸውም በላይ ከፍተኛ መስዋእትነት እስከመክፈል ደረጃ ደርሰዋል ነው የተባለው፡፡የእነሱ መሰዋትነት  “በጋራ የጀመርነውን ስራ አክብረን ለመቀጠል፤ ፍላጎታቸውን ለማክበር የበለጠ ቁርጠኝነት እንዲሰማን  ያደርገናል፡፡ ”

 7ሺህ 800 ካሬ ኪ.ሜ. ስፋት ባለውና በአስደናቂ መልከዓ ምድር በታጀበው ፓርክ  ውስጥ  እሳተ ገሞራዎች፣ ሰፋፊ ሀይቆች፣ ደንና  ማራኪ ተራራማ መልካ ምድር ያለው ሲሆን ፓርክ አመቱን ሙሉ  ዝናብ  ያገኛል፡፡

ፓርኩ የተቋቋመው ባለፉት አስር ዓመታት ቁጥራቸው እየጨመረ  የሚገኙት የተራራ  ጎሪላዎችን  ለመከላከል ከ 100 ዓመታት በፊት ነው፡፡"የዚህ ብሔራዊ ፓርክ  ታሪክ በእርስ በእርስ ጦርነት የተጎዳ የኮንጎ ግዛት አካል ነው፤እጅግ ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩት ፤ በጣም ብዙ መከራ ደርሶብናል፤ ግን ይህንን ፓርክ በሕይወት ማቆየቱ አስገራሚ ስኬት መሆኑን የፓርኩ ሐይቆች ኃላፊ የሆኑት ግራፊየን ሙይሳ ሲቫንዛ ይገለጹሉ፡፡

ሃላፊው አክለውም  የዲሞክራቲክ  ሪፖብሊክ  ኮንጎ  የተፈጥሮ ሀብት በምዕራባዊ  አውሮፓ  ገበያ  በስፋት  የሚፈለግ ነው፡፡   የአገሪቱ  የተፈጥሮ ሃብት ከየትኛውም አገር የበለጠ የአልማዝ ፣ የዘይት ፣ የኮባልትና የመዳብ ሀብቶች አሏት ፡፡

የተፈጥሮ ሃብቷ የኤሌክትሪክ መኪናዎች እና የስማርት ስልኮችን ለማምረት  የሚያስችሉ  ማዕድናት ይገኙበታል፡፡ ቨርንጋጋ ፓርክም እነዚህ የመሳሰሉ ማዕድናት ያሉት ነው፡፡ ከመሬት በታች እንዲሁም በተፈጥሮ እና በዱር እንስሳት ሀብቶች የበለፀገ ነው ፡፡

በአንድ ወቅት ሶኮ ተብሎ የሚጠራ አንድ  የእንግሊዝ  የነዳጅ  ኩባንያ  ከፓርኩ  ውስጥ  ማዕድን  ለማውጣት በኪንሻሳ መንግስት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም በአከባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት አላመው ሊሳካ ያልቻለ መሆኑን  ይጠቁማል፡፡

 ፓርኩና የፓርኩ አከባቢው በማዕድን ሀብት የታደለ ቢሆንም በፓርኩ አከባቢ የሚኖሩት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ገቢያቸው በቀን ከ 1.50 ዶላር በታች  ነው ፡፡ በታሪክ ውስጥ ካሉት  ከባድ ችግር አንዱ የእርስ በእርስ ጦርነቶች ነው፡፡ የእርስ በርስ ጦርነት ባለበት አገር የኢኮኖሚ ችግር ማሸነፍ ከባድ  መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡

በአንጻራዊነት ሰላም ያለት ጎረቤት አገር ሩዋንዳን በዓመት ከ 500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ቱሪዝምን ለመሳብ ስኬታማ ስራ ሰርታለች፡፡ በኬንያ ወደ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የቱሪዚም ኢንዱስትሪ አለ፡፡ "ይህ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ብሔራዊ በጀት የበለጠ ነው"

በቨርንጋ ውስጥ ቱሪዚም መጨመር  ፓርኩ  ለሌሎች የኢንቨስትመንት  ፕሮጀክቶች ለመሳብ ያግዛል፡፡

በፓርኩ ቅድሚያ ተስጥቶት ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ አንደኛው የፓርኩ ከፍተኛ ዝናብ እና ፈጣን ፍሰት ያላቸው ወንዞችን የሃይድሮ ኤሌክትሪክ  ለማመንጨት  የሚያስችል  ስራ  ተግባራዊ  ሁነዋል፡፡ ከፓርኩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉ አነስተኛ  ንግዶችን  በዙሪያው  እንዲጀመር  አድርጓል” ብለዋል ፡፡

በእነዚህ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ መርሃግብሮች አማካይነት በምናመነጨው እያንዳንዱ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል   ከ 800 እስከ 1000 የሚደርሱ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ችለናል  ነው ያሉት፡፡

በፓርኩ ዙሪያ ዛሬ በዚህ መንገድ የተፈጠሩ ወደ 12,ሺህ  ያህል የሥራ ቦታዎች አሉ ፣ ከእነዚህም ውስጥ ከ 1 ሺህ በላይ የሚሆኑት የታጠቁ  ቡድኖችን  የቀድሞ  ታጋዮች  ናቸው፡፡

የወጣት ሥራ አጥነት በ 70% በሚቀመጥበት የአፍሪካ አህጉር ላይ ሁከትን ለማሸነፍ ይህ መንገድ የተሸለና የተቻለ አመራጭ ነው ሲል የዘገባው አልጀዚራ  ነው ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም