የብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የፖለቲካ ፓርቲዎች አራተኛው የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24/2013 ( ኢዜአ) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አራተኛው ተከታታይ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።


በውይይቱ የምርጫ ምልክት የወሰዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችና የምርጫ ቦርድ አመራሮች ተገኝተዋል።

ውይይቱ በዋናነት የዕጩዎች ምዘገባ ሂደት ያለበት ሁኔታ፣ የቀረቡ አቤቱታዎችና የተሰጡ የመፍትሄ ምላሾች የሚዳስስ እንደሆነ ተገልጿል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመረጃ ማዕከል እንዲሁም የአጭር መልዕክት አሰራሮችም በውይይቱ ይዳሰሳሉ ተብሏል።

በቀጣይ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም የመራጮች ምዝገባና የአስፈጻሚዎች መረጃን ጨምሮ በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም