18ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርት ውድድርና 14ኛው ባህል ስፖርት ፌስቲቫል በድሬዳዋ ተጀመረ

70

ድሬዳዋ የካቲት 21//2013 (ኢዜአ)18ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፓርት ወድድርችና የ14ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ድሬደዋ ከተማ ተጀመረ።

የባህል ሰፖርት ውድድርና ፌስቲቫሉ  የተከፈተው በሰልፍ ትዕይንት ነው።

የድሬደዋ አስተዳደርና ፌደራል ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች፣ የስፖርቱ ማህበረሰብ አባላትና የድሬዳዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ውድድርና ፌስቲቫሉ ተጀምሯል።

የየክልሎች የባህል ስፖርትና ፌስቲቫል  ልዑካን ቡድኞች በክብር እንግዶች ፊት በማለፍ ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን አካባቢያቸውን ባህል የሚያንጸባርቁ ትእይንቶችን አሳይተዋል ።

የባህል ወድድሩና ፌስቲቫሉ ከአድዋ 125ኛው የድል በአል እየተከበረ ባለበት ወቅት መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው የተሳታፊ ክልሎች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም