የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር መቀሌ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር መቀሌ ገቡ
የካቲት 21/2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦሪዲን በድሪ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መቀሌ ገቡ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦሪዲን በድሪን የያዘው ልኡካን ወደ መቀሌ ያቀኑት በህግ ማስከበሩ ሂደት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡
ልኡካኑ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የካቢኔያቸው አባላት፣ የመቀሌ ከተማ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በሁለቱም የመንግስት አመራሮች የሚመራው ልኡክ በቆይታው ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡