በኮምቦልቻ ከተማ ተተኳሽ ጥይቶች ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

60

ደሴ፤ የካቲት 20/2013( ኢዜአ) በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሁለት ሺህ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይቶችን ሸሽገው በድብቅ ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የታክቲክ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥይቶቹን ትናንት  በከተማው ቀበሌ ሶሰት አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በድብቅ ሲገበያዩ እጅ ከፍንጅ ተደርሶባቸው ነው።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረትም ሻጭ፣ ደላላ እና ገዥ በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስረድተዋል።

አስፈላጊውን ማጠራት በማድረግ ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኙም ይደረጋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ለሀገር አንድነትና ሰላም ሲባል ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሆን ህገ ወጥ ተግባራት በማጋለጥ እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮማንደር አሊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም