በአዲስ አበባ ከተማ የላፍቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ከተማ የላፍቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2013(ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ548 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የላፍቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ ተጀመረ።
ግንባታውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የጤና ሚስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስጀምረውታል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገነባው ሆስፒታል ግንባታው በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።
ሆስፒታሉ 374 አልጋ የሚኖሩት ሲሆን፣ ለ1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል።
በከተማዋ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ግንባታውን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እንደሚያካሂድ ተገልጿል።
ሆስፒታሉን ለመገንባት ከሰባት ዓመት በፊት የመሰረት ድንጋይ ቢቀመጥም ግንባታ ሳይጀመር እስካሁን ቆይቷል።