በመቀሌ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ ሃይል ተመልሶ አገልግሎት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በመቀሌ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ ሃይል ተመልሶ አገልግሎት ጀመረ
የካቲት 17 ቀን 2013 (ኢዜአ) በመቀሌ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ ሃይል ተመልሶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ከስፍራው በተገኘው መረጃ መሰረት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የተፈጸመው ጉዳት ተጠግኖ ለአገልግሎት እንዲበቃ ተደርጓል።
ከየካቲት 9 ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተመልሷል።
ሌሎች ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ እየተሰራ ሲሆን ከሰሞኑ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ኢዜአ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
የህወሃት ጁንታ ርዝራዦች አዲጉዶም በተባለ አካባቢ ከአላማጣ - መሆኒ - መቐለ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረሱት የማበላሸት ተግባር በመላው ትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጹ ይታወሳል።