የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ለሕዳሴ ግድብ የአምስት ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዛ - ኢዜአ አማርኛ
የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ለሕዳሴ ግድብ የአምስት ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዛ
የካቲት 16 /2013 (ኢዜአ) የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የአምስት ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዛ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ “ግድቡ ለአገርና ለወገን የሚተርፍና ለትውልድ አሻራ የሚያስቀምጥ ትልቅ ስራ ነው” ብለዋል።
“ከዚህም አኳያ ለሕዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት የዚህ ትልቅ ታሪክ ባለቤት ናቸው” በማለት ገልጸው፤ እያደረጉት ላለው ድጋፍም ምስጋናቸ አቅርበዋል።
የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዋና ዋኬ ተቋሙ ለግድቡ ግንባታ የቦንድ ግዢ ሲፈጽም ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንና በቀጣይም ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።