ቀጥታ፡

ቻይና በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን መልሶ የማቋቋም ተግባር እንደምትደግፍ አስታወቀች

የካቲት 16/2013 (ኢዜአ) ቻይና በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው መልሶ የማቋቋምና ሰብአዊ እርዳታ መሰረታዊ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን እንደምታደርግ አስታውቃለች።

ድጋፉ ሩዝና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ ምግቦችን ያካተተ ነው ተብሏል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ዋንግ ዌንቢን ቻይና ለኢትዮጵያ ጥሩ ወዳጅ መሆኗን ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ትግራይ ክልልን ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ብልጽግናን እንዲያገኙ እንሰራለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ ላሉት ዜጎች እርዳታ እና ድጋፍ በመስጠት እና የአካባቢን ህይወት ወደነበረበት ለመመለስ እያደረገ ያለውን ጥረት እንደግፋለን ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም ቻይና በትግራይ ክልል መደበኛ ኑሮ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ የበለጠ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ነው የተናገሩት።

ዋንግ ዌንቢን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የበለጠ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ፒዩፕልስ ቻይና ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም