ኢትዮጵያዊያንን ለመከፋፈል በውስጥና በውጭ ጠላቶች የተደረጉ ሙከራዎች ከሽፈዋል - የአርበኞች ቤተሰቦች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያዊያንን ለመከፋፈል በውስጥና በውጭ ጠላቶች የተደረጉ ሙከራዎች ከሽፈዋል - የአርበኞች ቤተሰቦች
የካቲት 15/2013 (ኢዜአ) በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያዊያንን ለመከፋፈል በውስጥም ሆነ በውጭ ጠላቶች የተደረጉ ሙከራዎች መክሸፋቸውን የጀግኖች አርበኞች ቤተሰቦች ተናገሩ።
ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል ለመለወጥ እያደረጉ ያሉትን ጥረትም አድንቀዋል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጀግኖች አርበኞች ቤተሰቦች የትኛውም አገር ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚመነጩ ችግሮች እንደሚያጋጥሙት ይናገራሉ።
ችግሮቹ የሚፈጠሩበትና የሚፈቱባቸው መንገዶች የተለያዩ ቢሆኑም፤ ከችግር የጸዳ አገር አለመኖሩን በየዕለቱ በመገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ ዘገባዎች ምስክር መሆናቸውን በመጥቀስ።
የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ በኢትዮጵያ የሚፈጠሩ ችግሮች እንዲጋነኑና የዓለምን ትኩረት እንዲስቡ ለማድረግ የውስጥም የውጭም ኃይሎች ሲጥሩ ቆይተዋል ይላሉ።
ጥረታቸው የአገሪቷን ገጽታ ለማበላሸትና ካደጉት አገራት ምፅዋት ተቀባይነት እንዳትወጣ ካላቸው ፍላጎት እንደሚመነጭ ነው የተናገሩት።
ይሁንና ኢትዮጵያዊያን የተለያየ ዘር፣ ቀለም፣ ቋንቋና ብሄር ባለቤት ቢሆኑም፤ ብዝሃነታቸው አገራቸውን ከየትኛውም ጠላት ለመጠበቅ አላዳገታቸውም ብለዋል ልጅ ዳንኤል።
ለዚህ ደግሞ በ1888 አድዋ ላይ የተመዘገበው ድል ትልቅ ማሳያ ነው ይላሉ።
የአርበኞች ቤተሰቦቹ ወይዘሮ አልማዝ አንበርብርና ወይዘሮ ሳባ በላይም አያት ቅድመ አያቶቻችን በአገር ጉዳይ አንድ አቋም ይዘው በከፍተኛ መስዋትነት ያቆዩልንን አገር በማይረባ ምክንያት ከፋፍለን ታሪክ አናበላሽም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የቀደምት አባቶች ገድል ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለመላ ዓለም ትምህርት የሰጠ በመሆኑ አገር ተረ
ካቢው ትውልድ ታሪኩን አስጠብቆ የተሻለች አገር ለመገንባት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
የጀግኖች አርበኞች ቤተሰቦቹ ወጣቱ የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል የተሻለ ለማድረግ በትምህርትና በሥራ እያደረገ ያለውን ጥረትም አድንቀዋል።
ዘመኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንደመሆኑ በዕውቀትና በጥበብ የተገነባ ትውልድ የተሻለ ሥራ በማከናወን ኢትዮጵያን አንገቷን ከደፋችበት ድህነት አውጥቶ በክብር ቀና እንደሚያደርጋት እምነታቸውን ገልጸዋል።
ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፡-
ኢትዮጵያዊያን የኢጣሊያን ወራሪ ኃይል አድዋ ላይ ድል የመቱበት 125ኛ ዓመት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።