ሸነን ጊቤ የተሰኘ መጽሀፍ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
ሸነን ጊቤ የተሰኘ መጽሀፍ ተመረቀ

ጅማ ፣የካቲት 14/ 2013 (ኢዜአ)- ሸነን ጊቤ የተሰኘ መጽሀፍ በጅማ ከተማ ተመረቀ፡፡
በኢንጅነር ጋሊ አባ ቦር የተጻፈዉ ይህ መጽሀፍ በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጀ ሲሆን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ አዳራሽ ትላንት ተመርቋል፡፡
መጽሀፉ አምስት ምእራፎችና 400 ገጾች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያዊቹ ሁለት ምእራፎች ባጠቃላይ የኦሮሞ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡
"የተቀሩት ሶስት ምእራፎች ደግሞ በአምስቱ የጊቤ መንግስታት ታሪክ ላይ ያተኩራል" ሲል የመጽሀፉ ደራሲ ኢነጀነር ጋሊ አባ ቦር ለኢዜአ ተናግሯል፡፡
ወጣቱ የሀገሩን ታሪክ በጠራ ሁኔታ መረዳት ይችል ዘንድ ታስቦ የተጻፈ መጽሀፍ መሆኑንም ደራሲዉ ተናገሯል፡፡
በመጽሀፉ ምረቃ ላይ የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ እና የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር ተገኝተዋል፡፡