ቀጥታ፡

ባንኩ በስድስት ወራት ያከናወናቸው ዋና ዋና የማሻሻያ ስራዎች ትርፋማነቱን ለማሳደግ አስችሎታል ... የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት ያከናወናቸው ዋና ዋና የማሻሻያ ስራዎች ትርፋማነቱ ለማሳደግ እንዳስቻሉት ተገልጿል፡፡

የባንኩ የማሻሻያ ስራዎች መልካም አፈፃፀም ቀጣይነታቸው እንዲረጋገጥ በትኩረት መሰራት እንደሚያስፈልግ የጠቁሟል ።

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በተመራ ግምገማ ላይ እንደተገለጸው ባንኩ ትርፋማነቱ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 304.16 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለውና በ150 በመቶ ከፍ ጭማሪ አሳይቷል።

የባንኩ ትርፋማነት የተገኘው የተለያዩ የለውጥ ስራዎች በመተግበራቸው እንደሆነ ሚኒስትሩ በግምገማው ወቅት አብራርተዋል::

በተለይም ባንኩ የነበረውን ብድር የማስተዳደርና የመቆጣጠር አቅም ማሳደጉ ለዚህ ውጤት እንዳበቃው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልማት ባንክ በስድስት ወር ውስጥ የህዳሴ ግድብ ቁጠባን 500 ሚሊየን ለመፈፀም አቅዶ 883ነጥብ 47 ሚሊየን ብር ለመሰበብሰብ መቻሉ የሚበረታታ መሆኑን በግምገማው ወቅት ተነስቷል።

በተለይም ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው አቅም እየገነቡት ያለው የህዳሴ ግድብ ወቅቱን ጠብቆ ማጠናቀቅ እንዲቻል ባንኩ ጥረቱን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አቶ አህመድ ሽዴ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማሻሻያ ስራዎች ውጤታማነታቸውን ቀጣይ ለማድረግ ባንኩ በአዳዲስ እና በቴክኖሎጂ የታገዙ የአሰራር ስርዓቶችን ማጎልበት እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው፡፡

የባንኩን የውጭ ምንዛሬ አቅም ለማሳደግ እና የባንኩን አማራጭ የሀብት ምንጭ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ቀዳሚ ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ በዘላቂነት ከሀብት ጥገኝነት ለማውጣት የማሻሻያ ስራዎች በወጣላቸው መርሀ ግብር መሰረት መተግበር እንደሚኖርባቸው ማሳሰባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም