ንጉስ አባጅፋር በአድዋ ድል በነበራቸው አስተዋጻ ታሪክ ይዘክራቸዋል-- በጅማ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎች

ጂማ፣ የካቲት 12/2013(ኢዜአ) -የጅማው ንጉስ አባጅፋር በአድዋ ድል በነበራቸው አስተዋጽዎ በታሪክ እንዲታወሱ አድርጓቸዋል ሲሉ በጅማ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ፡

የጅማ ሙዝየም ሀላፊና የታሪክ ምህሩ አቶ ነጂብ አባ ራያ ለኢዜአ እንደገለጹት ንጉሱ ለአድዋ ጦርነት 550 ወታደሮችን ሲልኩ 60ሺህ ማርትሬዛ የገንዘብ ድጋፍም አድርገዋል፡፡

አባቶቻችን አድዋ ላይ ጠላትን ድባቅ የመቱት አንድነታቸውን ጠብቀው ስለኖሩና አንድነት ሀይል መሆኑ ስለገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"ኢትዮጵያውያን ጀግኞች አባቶቻችን ዘመናዊ መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ድል ያደረጉት በህብረት ስለቆሙ ነው" ብለዋል አቶ ነጂብ፡፡

ንጉስ አባ ጅፋር ለማዕከላዊ መንግስቱ መጠንከር ቀናኢ አመለካከት ነበራቸው” ያለው ደግሞ ጋዜጠኛ ተስፋዬ አየለ ነው ፡፡

አባ ጅፋር አፄ ምኒሊክ ባደረጉት ጥሪ መሰረት ጦራቸውን ይዘው ወደ ማዕከላዊ መንግስት ሄደው እሳቸውም አብረው ለመዝመት እንደወሰኑ ለንጉስ ምኒሊክ የነገሯቸው መሆኑን ታሪክ በማጣቀስ ተናግሯል ።

“ንጉስ ምኒሊክ ግን አባ ጅፋር መዝመት እንደሌለባቸውና ያስተዳደር ስራዎችን እንዳሰሩ ብሎም ማዕከላዊ መንግስቱን እንዲጠበቁ በማለት ጦራቸውን ብቻ እንዲዘምቱ አድርገዋል “ብሏል፡፡

“ንጉሱ በሳል የዲኘሎማሲ ሰው ስለነበሩ ለማዕከላዊ መንግስቱ መጠንከርና ለኢትዮጵያ አንድነት ጽኑ አቋማቸውን ለሚኒሊክ አሳይተዋል” ብሏል ጋዜጠኛ ተስፋየ።

እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ ገለጻ ንጉስ አባጅፋር በአድዋ ድል በነበራቸው አሰተዋጻ ታሪክ ይዘክራቸዋል።

አቶ መሐመድ አዱራ በበኩላቸው አባ ጁፋር ለአድዋ ጦር ማዝመት ብቻ ሳይሆን ለወታደሩ ቀለብም ይሰፍሩ ነበር፡፡

አባ ጅፋር በነበራቸው መልካም የውጭና የውስጥ ግንኙነት ለሀገር ሰላምና አንድነት በጐ አስተዋጽዎ እንደነበራቸው ተናግረዋል፡፡

አባት አርበኛ ሻንበል ንጉሴ ገሰሰ በበኩላቸው "ኢትዮጰያዊያን ጀግኖች አባቶች ጠላትን ከገባበት ገብተው ያርበደበዱት በሀገራቸው ጉዳይ እንደ አለት የጠነከረ አንድነት ስለነበራችው ነው" ብልዋል፡፡

አባቶቻችን አድዋ ላይ ጠላትን ድባቅ የመቱት አንድነታቸውን ጠብቀው ስለኖሩና አንድነት ሀይል መሆኑ ስለገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚያን ዘመን አባቶቻችን የነበራቸው ዋነኛው መሳሪያቸው ህብረታቸው ስለነበር አለም እስኪደመም ድረስ የነጭን ወራሪ ሀይል የውርደት ካባ አከናንበው ወደ መጣበት እንደመለሱት ተናግረዋል።

“ድር ብያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ አንድነት የማይቻል የሚመስለውን የሚያስችል የህልውና ትጥቅ ነው" ብለዋል፡፡

አርበኛው ሻንበል ንጉሴ ዛሬም ኢትዮጵያውያን የቀደመው አንድነታቸውን ጠብቀው ለሀገር ዘብ መቆም አለባቸው" ሲሉ መክረዋል፡፡

“በርግጥ ለሶሰት አስርት አመታት ወጣቱ በሀገሩ ጉዳይ አንድ ወጥ አመለካከት እንዳይኖረው መደረጉ ይታወቃል፤ ይሀን አሉታዊ እሳቤ ከውጣቱ አእምሮ ማጠብ ያስፈልጋል" ሲሉ በአጽእኖት ተናግረዋል፡፡

"ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች መከፋፈልና መገፋፋት የሚመጥን ስብእና አይደልም፤ በምንም መልኩ መከፋፈል አሸናፊ አያደርግም" ሲሉም አክለዋል፡፡

"ወጣት ወንድሙ ለገሰ በበኩሉ እኛ ወጣቶች ያባቶቻችንን ፈለግ በመከተል በአንድነት የጀግንነትና የድል አድራጊነት ወኔያቸውን ልንላበስ ይገባል" ብሏል፡፡

መተባበርና አንድነት ሀይል መሆኑን ተረድተን ህብረታችንን ማጠንከር አለብን" ያለው ወጣቱ አድዋ “የጀግንነታችን ምልክት የአንድነታችን አርማ በመሆኑ ስንዘክረው እንኖራለን” ሲል አስታውቋል፡፡

በጅማ ከተማም የ125ኛውን የአድዋ የድል በአል ለማክበር ከከተማው አስተዳደር ጋር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም