የደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ነዋሪዎች የዶክተር አብይ የለውጥ መንግስት በመደገፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ነዋሪዎች የዶክተር አብይ የለውጥ መንግስት በመደገፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው
ደሴ፤ የካቲት 9/2013 (ኢዜአ) በበደቡብ ወሎ ዞን የደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ነዋሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የለውጥ መንግስትን በመደገፍ ሠላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ ነው።
በድጋፍ ሠልፉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት እየተሳተፉ ነው።
የድጋፍ ሠልፉ በደሴ ከተማ ሰኞ፣ አራዳ፣ ሆጤ፣ ቧንቧ፣ መናፈሻ ክፍለ ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።
ሠልፈኞቹ ወደ ሆጤ ስታድዮም በማምራት የተለያዩ የድጋፍ መልዕክቶችን በማሰማት ላይ ናቸው።
በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ከተማ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተንቀሳቀሱ ነዋሪዎች በዋና ዋና መንገዶች በመዘዋዋር ድጋፋቸውን እየገለጹ ሲሆን ወደ ኮምቦልቻ ስታዲዮም በማቅናት መረሃ ግብሩ እዚያው እንደሚጠናቀቅ ታውቃል።
በሁለቱም ከተማች እየተካሄደ ባለው ሠልፍ ነዋሪዎቹ እያሰሟቸው ካሉት መፈክሮች መካከል ለውጡን እንደግፋለን፣አንድነታችንንና ሠላማችንን አጠናክረን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እናስጠብቃለን ፣ የዶክተር አብይንና ካቢኒያቸወን እንደግፋለን፣ የተሸረሸረውን የኢትዮጰያዊነት ባህልና እሴት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት እናደንቃለን የሚሉ ይገኙበታል።