ለጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ አባላት የገንዘብ ሽልማት ተበረከተ - ኢዜአ አማርኛ
ለጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ አባላት የገንዘብ ሽልማት ተበረከተ
ጅማ ሃምሌ 19/2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ሻምፒዮን ለሆነው ለጅማ አባጅፋር ስፖርት ክለብ ተጨዋቾችና አሰልጣኞች አንድ ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ሽልማት ተበረከተ። በጅማ ከተማ አስተዳደር የተበረከተው የገንዘብ ሽልማት ትላንት ምሽት በጅማው ሴንትራል ሆቴል በተዘጋጀው የእራት ግብዣና የምስጋና ስነስርዓት ወቅት ተሰጥቷል። የጅማ አባጅፈር እግር ኳስ ክለብ ፕሬዘዳንት አቶ ዳንኤል አለሙ በዚህ ወቅት "ክለባቸው ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተቀላቃለበት የመጀመሪያው ዓመት አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሰርቷል "ብለዋል። ውጤቱ የተገኘው አሰልጣኙ፣ ተጫዋቾች፣ የክለቡ አመራር፣ደጋፊዎች፣ በከተማዋና ከከተማው ውጭ የሚገኙ ባለሃብቶች ባደረጉት የተቀናጀ ድጋፍ መሆኑ ተመልክቷል፡፡፡ ለክለቡ ውጤታማነት ቁልፍ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተጫዋቾችና አስልጣኞች አንድ ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ሽልማት ፣ የተሻለ አስተዋጽኦ ላደረጉ የሚዲያ አካላትና የክለቡ አመራሮች እውቅናና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል። ክለቡ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ሻምፒዮን ሊግ ላይ እንደሚካፈልና ለተገኘው ውጤቱ ቁልፍ ሚና የተጫወቱተን አሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በክለቡ አሰልጣኝነት እንደሚቆዩ ይጠበቃል። አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ ከጅማ አባጀፋር ጋር ያላቸውን የአንድ ዓመት ኮንትራት ያጠናቀቁ ሲሆን እስካሁን ድረስ በጅማ አባጀፋር ክለብ ለመቆየታቸወ አዲስ ኮንትራት ያለተፈራሩሙ መሆኑ ታውቋል።