ቀጥታ፡

ኢዜአ በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማውን ሃዘን ገለፀ

ሐምሌ 19/2010 የኢትዮጵ ዜና አገልግሎት ኤጄንሲ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡ ኤጄንሲው ለኢንጂነር ስመኘው ቤተሰቦች፣ ለፕሮጀክቱ ሰራተኞችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል። ኢንጂነር ስመኘው ህይወታቸው እስካለፈበት እለት ድረስ የታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው እያገለገሉ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ  ዛሬ ጠዋት በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ተዘግቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም