ቀጥታ፡

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ አስክሬን ወደ ሆስፒታል ተወስዷል

አዲስ አበባ ሐምሌ 19/2010 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አስክሬን ለምርመራ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተወስዷል። የሞታቸውን መንስኤ ለማጣራት የፖሊስ አባላት ምርመራ እያካሄዱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሆስፒታሉ ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤቱን ፖሊስ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል። ኢንጂነር ስመኘው ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር A29722 ቪ ኤይት መኪናቸው ውስጥ ነው መስቀል አደባባይ ሞተው የተገኙት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም