የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ13ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን አለም አቀፍ የሠላም አስከባሪዎችን እያስመረቀ ነው

173

ሁርሶ ፤ የካቲት 06/2013(ኢዜአ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በሠላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ13ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን አለም አቀፍ የሠላም አስከባሪዎችን እያሰመረቀ ነው።

ተመራቂዎቹ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚሠማሩ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ናቸው።

አለምአቀፍ ግዳጅን መወጣት የሚያስችላቸውን የሥልጠና ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የካቢኔ አባላት በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ፣ ሠላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ ባሻገር ለአፍሪካ እና ለሌላም አለም ሠላም ማስከበር ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሚገኙ ሁርሶ የሚገኘው ሪፖርተራችን ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም