ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአልጀርሱ የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር እስካሁን ስምንት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች

አዲስ አበባ ሀምሌ 19/2010 ኢትዮጵያ በአልጀሪያ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር እስካሁን ስምንት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በአልጀሪያ መዲና አልጀርስ ላይ እየተካሄደ ያለው 3ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ዘጠነኛ ቀኑን ይዟል። ኢትዮጵያም በዚህ ውድድር ላይ በስድስት የስፖርት አይነቶች እየተካለፈች ትገኛለች። ትናንት በስምተኛ ቀን ውሎ የተለያዩ የፍጻሜ ውድድሮች ሲደረጉ ኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ፣ አንድ የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች። የወርቅ ሜዳሊያዎቹ አትሌት አብረሀም ስሜ  በ 2 ሺህ  ሜትር መሰናክል ወንዶችና አትሌት ሂሩት መሸሻ በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር ነው የተገኙት። እንዲሁም በ 5 ሺህ ሴቶች ውድድር አትሌት ስንታየሁ ማስሬ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታገኝ አትሌት መለሰ ንብረት ደግሞ በ 1 ሺ 500 ሜትር ውድድር  ሶስተኛ በመውጣት ለሀገሩ  የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል። ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ እስካሁን በብስክሌት፣ በአትሌቲክስ ስፖርትና በወርልድ ቴኳንዶ ያስመዘገበችው ስምንት የወርቅ ሜዲሊያን ጨምሮ 16 ሜዳሊያዎችን በመሰብስብ በደረጃ ሰንጠረዡ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በዛሬው እለትም የካራቴ ስፖርትን ጨምሮ በአትሌቲክስና በቦክስ የስፖርት አይነቶች  የፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች ቀጥለው እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል።              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም