የኦሮሚያ ክልል እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች ጅማ ገቡ

ጅማ፣የካቲት 05/2013 (ኢዜአ)፡- የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በጅማ ዪነቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት ጅማ ከተማ ገቡ፡፡

ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ  አባ ጅፋር አውሮፕላን  ማረፍያ ሲደርሱ የጅማ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር እና የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱላኪም ሙሉ አቀባብል አድርገውላቸዋል፡፡

ከአቀባበሉ በኋላም በጅማ ዞን  ወደ ሰቃ ወረዳ በማቅናት  የግብርና ልማት እንቅስቅሴን በመስክ መመልከታቸውን የወረዳው  ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት  ሀላፊ አቶ አብዶ መሐመድ ገልጸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና  ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ  ነገ በሚካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚገኙም የጅማ ዩኒቨርሲቲ  የውጭ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን  ሲኒየር ዳይሬክተር ዶክተር ወንድሙ ለገሰ ማሳወቃቸውን ጅማ የሚገኘው የኢዜአ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም