ቀጥታ፡

የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው

አርባ ምንጭ፤ የካቲት 3/2013(ኢዜአ) በጋሞ ዞን የአርባምንጭ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ ሠላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ ነው።

ነዋሪዎቹ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ወደ አርባምንጭ ሁለገብ ስታዲዮም በማምራት ላይ ይገኛሉ።

ሠልፈኞቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተሰጠው በሳል አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥና የብልጽግና ጉዞ እንደሚደግፉ የሚገልጽ መፈክር እያስተጋቡ ነው።

ብልጽግናን በጋራ ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቅሴ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ የሚጥሩትን የሚያወግዝ እና ለግድቡ ግንባታ ስኬታማነት ማንኛውም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን እየገለጹ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም