የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ የዜጎችን ተጠቃሚነትን ያማከለ መሆን አለበት ተባለ - ኢዜአ አማርኛ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ የዜጎችን ተጠቃሚነትን ያማከለ መሆን አለበት ተባለ
አዲስ አበባ ሀምሌ 18/2010 በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች መብት መጠበቅ እንዳለበትና አዳዲስ ፓርኮችን ለማልማት ሲባል ከየአካባቢው ለሚነሱ ዜጎች ተገቢው ካሳ ሊሰጥ እንደሚገባ የማዕረግ ተመራቂ ተማሪዎች ጠቆሙ። በዘንድሮ ዓመት የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች ዛሬ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል። በዚሁ ወቅት በተካሄደው ውይይት ምሩቃኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለአገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ለውጥ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው የፓርኮቹ ልማት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በሁሉም ክልሎች የሚስፋፋበት ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በፓርኮቹ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ክፍያና ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ ያለው ክፍተት እንዲስተካከል ምሩቃኑ ጠይቀዋል። በፓርኮቹ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ከውጪ ከሚመጡ ባለሙያዎች ያልተናነሰ እውቀትና ክህሎት እያላቸው ከውጭ ዜጎች በጣም ዝቅተኛ ክፍያ መቀጠራቸው አግባብ አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል። “ለኢንዱትሪ ፓርኮች ግንባታ ተብሎ ከአየካባቢው የሚነሱት አርሶ አደሮች ተገቢውን ካሳ እየተከፈለው አይደለም'' ያሉት ምሩቃኑ ፓርኮቹ በህብረተሰቡ ላይ የኢኮኖሚ ጉዳት ማስከተላቸውን ገልፀዋል። ከዚህም ሌላ ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በሚገነቡበት አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በፓርኩ መገንባት የመጀመሪያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠር እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶች ለውጭ ገበያ ብቻ የሚቀርቡበት ምክንያት ሊጤን ይገባል ሲሉ ተማሪዎቹ አንስተዋል። የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን በሰጡት ማብራሪያ ከተመራቂ ተማሪዎቹ የተነሱት ሃሳቦቹ ትክክል መሆናቸውን ጠቅሰው “ችግሮቹን ለማቃለል እየተሰራ ነው'' ብለዋል። ከሰራተኛ ደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር ተያይዞ የሚታዩት ችግሮች የሚፈቱት ምርታማነትን በማሳደግ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሽፈራው ምርቶችን ለአገር ውስጥ ፍጆታ ለማዋል ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬን በማሳደግ ካፒታል ማጠራቀም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። ፓርኮቹ አገሪቱ በአለም ላይ እውቅና እንድታገኝ ያስቻለ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው የሚታዩት ችግሮች ከፓርኮቹ መስፋፋትና ምርታማነት ማደግ ጋር ተያይዘው እንደሚፈቱ ገልጸዋል። ገና እያደገ ባለ ኢንዱስትሪ ማህበራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ማስገደድ ባይቻልም ኩባንያዎቹ ዓለም ዓቀፍ በመሆናቸው ለስማቸው ሲሉ የሚሰሩት እንደሆነም ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ ለኢንዱስትሪው እድገት ተስፋ በመሆናቸው ለዘርፉ የድርሻቸውን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ሽፈራው አሳስበዋል። ምሩቃኑ በጉብኝታቸው ደስ መሰኘታቸውን ገልፀዋል። በፓርኩ ያዩት ነገር አገሪቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገት እያመጣች ስለመሆኑ ተጨባጭ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል። ሆኖም የተጠቀሱት ችግሮች ሲቀረፉ ህብረተሰቡ የበለጠ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል። በመጨረሻም የሜዳሊያ ተማሪዎቹ በስማቸው እንክብካቤ የሚደረግለት ችግኝ በፓርኩ አካባቢ በመትከል ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በአሁኑ ወቅት አስራ አንድ አምራች ኩባንያዎች የማምረት ሥራ የጀመሩ ሲሆን ለ15 ሺህ ዜጎችም የስራ እድል ፈጥረዋል። የፓርኩ ምዕራፍ ሁለት ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ ለሌሎች 50 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል። በሁሉም ክልሎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን በቀጣይ በአሶሳና በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት መታቀዱ ተነግሯል። ዘንድሮ ከመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑ ከ400 በላይ ምሩቃን በተያዘላቸው መርሃ-ግብር መሰረት ፕሬዚዳንተ ዶክተር ሙላቱ ተሾመን እና ጠቅላይ ሚኒስተር ዓብይ አህመድን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር መድረክ ተፈጥሮ ውይይት አድርገዋል።