የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ሐረሪ ክልል ገባ - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ሐረሪ ክልል ገባ
ጥር 28/2013(ኢዜአ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሐረር ከተማ በተለምዶ ሀማሬሳ ከሚባለው አካባቢ ሲደርሰ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ቆይታውን አጠናቆ ወደ ሐረር የተጓዘው የታላቁ ሕዳሴ ዋንጫ በሐረሪ ክልል የሚከናወነውን የግድቡ ግንባታ የገቢ አሰባሰብ ለማሳደግ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ በነበረው ቆይታው ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደተሰበሰበ ለማወቅ ተችሏል።
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተማሪዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለዋንጫው አቀባበል አድርገዋል።