ቀጥታ፡

በአስራ አንደኛዉ ሳምንት በቤትኪንግ ሰበታ ከነማ አዳማ ከተማን 1 ለ ባዶ አሸነፈ

ጅማ፣ ጥር 27/2013(ኢዜአ ) በአስራ አንደኛዉ ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ 9 ሰዓት ላይ በተደረገዉ ጨዋታ ሰበታ ከነማ አዳማ ከተማን 1ለባዶ አሸነፈ፡፡

ሁለቱም ክለቦች በደረጃ ሰንጠረዡ በመጨረሻዉ ረድፍ የሚገኙ ሲሆን ሰበታ ዛሬ አዳማን 1ለ 0 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ አግኝቶ ነጥቡን አስር በማድረግ 11 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

አዳማ ከነማ በ7 ነጥብ ጅማ አባ ጅፋር በ4 ነጥብ የመጨረሻዉ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

በነገዉ እለት ረፋድ 4 ሰአት ወልቂጤ ከነማ ከሀዋሳ ከተማ እንዲሁም 9 ሰአት ላይ ፋሲል ከነማ ከድሬድዋ ከነማ ይገናኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም